Tuesday, April 11, 2006

ድርሰት

ድረስ?

 

እኔ ነኛ ደራሲው

ያውም ግጥም ፀፊው?

እኔ መፍጠር የማልችለው

እግዜር እራሱን ብሆነው

ለምን ብዬ ልጉዳ ራሴን?

በሃሳብ ጎርፍ አእምሮየን?

ለዝና ነው ለመቅለያ?

መሳተፌ ከዚህ ሙያ?

ራሴን ሳምስ ከቀን ማታ

ለመጻፍ ስል ያን ጨዋታ

መጣ ስሜት?

ይ ልታገስ ምናለበት

ለዚያች ረቂቅ ለእንቁ ወቅት

ደራሲዎች ለሚያልሟት

የምን መጻፍ ማውራት ስችል

ፊደሎቹን ላመሳቅል

ጻፊ አይደለሁ ጽፈም አላውቅ

ሳላውቅ ሃገር እንዴት ልናፍቅ?

ፊነት ስጦታ ነው

ልሁን ማለት መላም የለው

ሲል ወቅሰኝ ህሊናዬ

ለራሴ ሲል ለጤናዬ

ከዚያ አንድ ቀን ተቀምጬ

በኑሮ ሃሳብ ተሰምጬ

ውጣ ውረድ ሳሰላስል

አየሩ ላይ አይኔም ትክል

ይሄ ኖሯል? ይው አልኩኝ

ሌሊት እንቅልፍ የነፈገኝ

ያ የስሜት የድርሰት ምንጭ

እንደ እጅ ውሃ የሚያሟልጭ

መጻፍ ጀመርኩ በደስታ

ላለኝ ስሜት ሳልሰጥ ፋታ

ያኔ ገባኝ ግልጽ ሆነልኝ

እንቆቅልሕ የሆነብኝ

ባያውቅ ነው እንጂ ሁሉም

ደራሲ ነው ባለው አቅም

የሚቀረን አንድ ነገር

ወረቀት ላይ ቃሉን ማስፈር

ጨረቓ

Posted by CHEREKA in 14:15:08 | Permalink | No Comments »